1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ አቤቱታ

ዓርብ፣ መጋቢት 9 2003

ኦህኮ አባላቶቹ እየታሰሩ እንደሆነ ይገልጻል። ሰላማዊ ትግሉን አላቋርጥም ይላል

https://p.dw.com/p/RAdC
ምስል picture alliance/dpa

ኢትዮጵያ ውስጥ፤ በኦሮሚያ መስተዳድር ፤ በተለያዩ ጊዜያት ፤ እስካሁን ከ 102 በላይ የሚሆኑ ቢሮዎቹ፤ በ ኢ ህ አ ዴግ መንግሥት እንደተዘጉበት የገለጠው የኦሮሞ ህዝብ ኮንግረስ ፣ ከዚህ ቀደም ያጋጥሙት ከነበሩት መሰናክሎች በተጨማሪ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ፤ቀድሞ የፓርላማ አባላት የነበሩና ታዋቂ አባላቱ ፣ ከየቦታው ፣ በፌደራል ፖሊስ እየተያዙ መታሠራቸው እየተነገረ ነው። «አሁን እየተወሰደ ያለው እርምጃ ፤ ድርጅታችንን ሙሉ በሙሉ ባገር ውስጥ ለመዝጋት የሚደረግ ጥረት ይመስላል» ያሉት የፓርቲው ዋና ጽ/ቤት ምክትል ኀላፊ አቶ ኦልባና ለሊሣ፤ የኢትዮጵያ ህዝብና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም ጉዳዩን በታዛቢነት እንዲከታተለው ጠይቀዋል። ድሮም፤ አሁንም ወደፊትም የኦሮሞ ህዝባዊ ኮንግረስ፤ ሰላማዊ ትግሉን እንደሚቀጥል ያስታወቁትን አቶ ኦልባናን ፣ ተክሌ የኋላ በስልክ አነጋግሮአቸዋል።

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሀመድ