የኦሮሚያ ወጣቶች ተቃዉሞና መድረክ
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 6 2008ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥት ለአዲስ አበባ ከተማ የነደፈዉን የማስፋፊያ ዕቅድ በተቃወሙ ሰዎች ላይ የሚወስደዉን የኃይል እርምጃ የኢትዮጵያ ፌደራዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ ባጭሩ) አወገዘ። የተለያዩ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ያሰባሰበዉ መድረክ ዛሬ ባወጣዉ በመግለጫዉ የአዲስ አበባን የማስፋፋት ዕቅድ «ሕገ-ወጥ» በማለት ተቃዉሞታል። ዕቅዱን በሚቃወሙ ወገኖች ላይ የመንግሥት የፀጥታ ሐይላት በወሰዱት እርምጃ በተለያዩ አካባቢዎች ከሰላሳ በላይ ሰዎች መገደላቸዉን፤ በመቶ የሚቆጠሩ መቁሠላቸዉንም መድረክ አስታዉቋል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ መግለጫዉን ተከታትሎ የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሠ