የኦሮሚያ መስተዳድር የባሕል ማዕከላት ግንባታ
ዓርብ፣ ነሐሴ 27 2003ማስታወቂያ
የኦሮሚያ መስተዳድር በርዕሠ-ከተማ አዲስ አባባ ጨምሮ በተለያዩ የመስተዳድሩ ከተሞች የኦሮሞ የባሕል ማዕከላትን እያስገነባ ነዉ።የመስተዳድሩ የቱሪዝም ቢሮ እንዳስታወቀዉ ማዕከላቱ የኦሮሞን ታሪክ፥ ቅርስ፥ ባሕልና አኗኗርን ለመጠበቅና ለሐገር ጎብኚዎች ለማስተዋወቅ ይጠቅማሉ።ከማዕከላቱ ሁሉ እጅግ ትልቁ አዲስ አባባ ዉስጥ የሚገነባዉ ነዉ።በቅርቡ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ የሚጠበቀዉ የአዲስ አባባዉ ግዙፍ የኦሮሞ የባሕል ማዕቀል ከሁለት መቶ አርባ ሚሊዮን በላይ ወጪ ተደርጎበታል።ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ