የእግር ኳስ ግጥሚያና ቅሌቱ
ረቡዕ፣ ጥር 29 2005ማስታወቂያ
በመላዉ ዓለም በየደረጃዉ ከሚደረጉ የእግር ኳስ ግጥሚያዎች የአብዛኞቹ ዉጤቶች ከግጥሚያዉ በፊት በቁማርተኞች እንደሚበየን ፖሊስ አጋለጠ።የአዉሮጳ ፖሊስ (ዩሮፖል) እንደሚለዉ የዓለም ተወዳጅ ስፖርት የእግር ኳስ ተጨዋቾች፥ ዳኞች፥ አሠልጣኖች፥ የክለብ ባለቤቶችና ባለሙያዎች ከቅሌት የተነከሩ ናቸዉ።ዩሮፖል ከሲንጋፑር በመላዉ ዓለም የተዘረጋዉን የቁማር መረብ ከሚመሩት ከአንዱ ያገኘዉን መረጃ ጠቅሶ እንዳስታወቀዉ የስድስት መቶ ሰማኒያ ግጥሚያዎችን ዉጤት ከየግጥሚያዎቹ በፊት የወሰኑት በዉርርድ ቁማር የከበሩ ቱጃሮች ናቸዉ።ከስድስት መቶ ሰማንያዎቹ ግጥሚያዎች ሰወስት መቶ ሰማኒያዎቹ አዉሮጳ፥ የተቀሩት አፍሪቃ፥ እስያና ደቡብ አሜሪካ የተደረጉ ናቸዉ።ሥለ ቅሌቱ የበርሊን ወኪላችን ይልማ ሐይለ-ሚካኤልን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።
ይልማ ሐይለ ሚካኤል
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ