1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእነ አቶ በረከት ስምዖን የፍርድ ቤት ዉሎ 

ዓርብ፣ ጥር 17 2011

አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ከእስር እንዲለቀቁ እና ጉዳያቸውም በአዲስ አበባ እንዲታይ ጥያቄ አቀረቡ። ጥያቄያቸውን አቃቤ-ሕግ ተቃውሟል። ሁለቱ የቀድሞ ጉምቱ ሹማምንት በእስር ቤት መሰደባቸውን፤ ምግብ እንዳልቀረበላቸው እና ቤተሰቦቻቸው ጉዳያቸውን ከመከታተል መከልከላቸውን ጠቅሰው አቤቱታ አቅርበዋል።

https://p.dw.com/p/3CCj2
Äthiopien Regierungsvertreter
ምስል DW/Tesfalem Waldyes

የአቶ በረከት እና አቶ ታደሰ የፍርድ ቤት ዉሎ

አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ከእስር እንዲለቀቁ እና ጉዳያቸውም በአዲስ አበባ እንዲታይ ጥያቄ አቀረቡ። ጥያቄያቸውን አቃቤ-ሕግ ተቃውሟል። ሁለቱ የቀድሞ ጉምቱ ሹማምንት በእስር ቤት መሰደባቸውን፤ ምግብ እንዳልቀረበላቸው እና ቤተሰቦቻቸው ጉዳያቸውን ከመከታተል መከልከላቸውን ጠቅሰው አቤቱታ አቅርበዋል።

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በባሕር ዳር ከተማ በእስር ላይ የሚገኙት አቶ በረከት ስምዖን እና አቶ ታደሰ ካሳ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት ቀረቡ። ተጠርጣሪዎቹ "ከእስር ተለቅቀን ክርክራችንን በውጭ እናድርግ" ሲሉ ቢጠይቁም አቃቤ ሕግ "ሰነድ ሊያጠፉብኝ ስለሚችሉ ጥያቂያቸውን እቃወማለሁ" ብሏል፡፡ ፍርድ ቤቱ ተጠርጣሪዎች ለየካቲት 1 ቀን 2011 ዓ.ም.  አንዲቀርቡና ወደ ማረሚያ ቤት አንዲወርዱ አዝዟል፡፡

አለምነኽ መኮንን

አዜብ ታደሰ 

እሸቴ በቀለ