የእስራኤል የፖሊስ አዛዥ አስተያየት
ሐሙስ፣ ነሐሴ 26 2008ማስታወቂያ
የእስራኤል የፖሊስ አዛዥ ሮኒ አልሼይሽ የአገሪቱ ጠበቆች ማህበር ባዘጋጀው ጉባኤ ላይ ላይ ለተጠየቁት ጥያቄ ሲመልሱ «በዓለም ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶች ወጣቶች እና ስደተኞች አለመመጠን በወንጀል ይሳተፋሉ» ብለዋል። የፖሊስ አዛዡ አስተያየት በቤተ-እስራኤላውያን እና በፖለቲከኞች ከፍተኛ ወቀሳ ቀስቅሶባቸዋል። ከስምንት ሚሊዮን ዜጎች 135,000 ቤተ-እስራኤላውያን ሲሆኑ 17 በመቶው ደግሞ የአረብ ዝርያ ያላቸው ናቸው። የፖሊስ አዛዡ በቤተ-እስራኤላውያን ጉዳይ ያልተመጣጠነ ኃይል ጥቅም ላይ መዋሉንም ተናግረዋል። ለወራት ጠንካራ የአደባባይ ተቃውሞ ያደረጉት ቤተ-እስራኤላውያን አሁንም የፖሊስ አዛዡ ከሥራቸው እንዲባረሩ በመጠየቅ ላይ ናቸው። ከእነዚህ መካከል ሶሻል ወርከር የሆኑት ወ/ሮ አማረች አለፈ ይገኙበታል።
እሸቴ በቀለ
አዜብ ታደሰ