የእስራኤል ኤምባሲዎች ሠራተኞች አድማ
ዓርብ፣ መጋቢት 19 2006ማስታወቂያ
በመላው ዓለም የሚገኙ የእስራኤል ኤምባሲዎች ሠራተኞች የመቱት የሥራ ማቆም አድማ ከእስራኤል በሚወጡና ወደ እስራኤል በሚሄዱ መንገደኞች እንቅስቃሴ ላይ ተፅእኖ እያደረገ ነው ። ካለፈው እሁድ አንስቶ ላላተወሰነ ጊዜ በመካሄድ ላይ ያለው ይኽው የሥራ ማቆም አድማ በእስራኤል ታሪክ የመጀመሪያው መሆኑ ተነግሯል ። የአድማው መንስኤ እነዚሁ የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሠራተኖች ያቀረቡት የደሞዝ ጭማሪ ና የሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች ጥያቄ መልስ አለማግኘቱ ነው ። ሠራተኞቹ ወደ ሁለት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ እነዚህን ጥያቄዎች ሲያቀርቡ ቆይተዋል ። ባለፉት ሰባት ወራት ወራት በጉዳዩ ላይ ከአስራኤል የገንዘብ ሚኒስቴር ጋር ድርድሮች ቢካሄዱም ባለፈው የካቲት 25 ፣ 2006 ዓም ያለ ውጤት አብቅቷል ። ስለ ሥራ ማቆም አድማውና ተፅእኖው የሃይፋ እስራኤል ወኪላችንን ግርማው አሻግሬን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬዋለሁ ።
ግርማው አሻግሬ
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሃመድ