የእስረኛዉ የረሐብ አድማ
ማክሰኞ፣ መጋቢት 24 2005ማስታወቂያ
በአሸባሪነት ክሥ አስራ-ሥምንት ዓመት እስራት ተበይኖባቸዉ ወሕኒ ቤት የሚገኙት የኢትዮጵያ መንግሥት ተቃዋሚ ፓርቲ የአመራር አባል አቶ ናትናኤል መኮንን የረሐብ አድማ መቱ።አቶ ናትናኤል አድማዉን የመቱን ቤተ ሠብ፥ ዘመድ እና ወዳጅ እንዳይጠይቃቸዉ፥ ምግብና አላቂ ቁሳቁስ እንዳይደርሳቸዉ የታሠሩበት የቂሊንጦ ወሕኒ ቤት ማገዱን በመቃወም ነዉ።የአቶ ናትናኤል ፓርቲ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ (አንድነት) የቂሊንጦ ወሕኒ ቤት እርምጃን ተቃዉሟል። ከቀድሞዉ የአንድነትና የመድረክ ከፍተኛ ባለሥልጣን ከአቶ አንዱ አለም አራጌ ጋር በአሸባሪነት የተከሰሱት አቶ ናትናኤል አስራ-ሥምንት ዓመት ተፈርዶባቸዉ ይግባኝ ብለዉ እየተሟገቱ ነዉ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ