የእርዳታ ቁሳቁስን የተመለከተው የስዊድኑ ተቋም ዘገባ
ረቡዕ፣ ሚያዝያ 13 2002ማስታወቂያ
ወደ ተለያዩ አገራት የእርዳታ ቁሳቁስ ጭነዉ የሚበሩ የእቃ ጫኛ አዉሮፕላኖች በህገ ወጥ መንገድ መሳርያ እና ዕጽ ማዘዋወራቸዉን ለመግታት ስዊድን ስቶኮልም የሚገኘዉ አለም አቀፉ የሰላም ምርምር ተቋም በእንግሊዘኛ ምህጻሩ SIPRI በድረ ገጹ የእርዳታ ቁሳቁስ የሚጭኑ የተለያዩ የእቃ ጫኝ አዉሮፕላን ድርጅቶች የሚጠቀሙበትን የስነ-ምግባር ረቂቅ ዉል ይፋ ማድረጉን ገልጾአል። ተቋሙ ከትናንት ጀምሮ በድረ ገጹ ይፋ ያደረገዉን ዉል ረቂቅ የእርዳታ ተቋሞችም ሆነ የእቃ አስጫኝ ድርጅቶች ሟሟላት የሚገባቸዉን ስነ-ምግባር ጠንቅቀዉ እንዲያዉቁ ነዉ።
Agnes Büring
አግነስ ቢውሪንግ/አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ