1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእርሻ ልማት ይዞታ በአፍሪቃ

ረቡዕ፣ ሰኔ 2 2002

ከሣሃራ በስተደቡብ የሚገኘው የአፍሪቃ ክፍል ዛሬም አያሌ ሕዝብ ከዝቅተኛው የድህነት መስፈርት በታች ኑሮውን የሚገፋበት የዓለም አካባቢ ነው።

https://p.dw.com/p/Nm6l
ምስል dpa

አብዛኛው ነዋሪ አርሶ አደር ሆኖ ሳለ የእርሻና የገጠሩ ልማት የሚገባውን ያህል እንዲራመድ አልተደረገም። የምግብ ዋስትና በሚገባ ባለመረጋገጡ ጥቂት እንኳ ዝናብ በጠፋ ቁጥር ኢትዮጵያን በመሳሰሉት አገሮች ለረሃብና ለረሃብ ሞት የሚጋለጡት ብዙዎች ናቸው።
ባለፉት ዓመታት በተከታታይ በአፍሪቃ ታየ የተባለው የኤኮኖሚ ዕድገትም የገጠሩን ልማት መሠረቱ ባለማድረጉ በብዙሃኑ የማሕበራዊ ኑሮ መሻሻል ሊከሰት አልቻለም። ያለፉት ሁለት ዓመታት ዓለምአቀፍ የኤኮኖሚ ቀውስ ደግሞ ድህነቱን ይበልጥ ሲያባብስ የኑሮ ውድነትና በተለይም የምግብ ዋጋ መናር ማሕበራዊ ቀውስን እንዳያስከትል ማስጋቱን ዛሬም የቀጠለ ጉዳይ ነው።
ለመሆኑ ከዚህ አዙሪት መውጣት የሚቻለው እንዴት ነው? የአፍሪቃን የእርሻና የገጠር ልማት እንዴት ለማሻሻል ይቻላል? ያለፉት ሰላሣ ዓመታት የሕዝባዊት ቻይና ልምድስ በእርያነት ሊወሰድ ይችላል ወይ? በነዚህና ከነዚሁ በተሳሰሩ ጥያቄዎች ላይ በዚህ በቦን ዩኒቨርሲቲ በእንስሳት ሣይንስ ተባባሪ ፕሮፌሰር የሆኑትን ኢትዮጵያዊ ባለሙያ ዶር/ዳዊት ተሥፋዬን አነጋግረናል፤ የቃለ-ምልልሱን የመጀመሪያ ክፍል አድምጡ።

መሥፍን መኮንን

ነጋሽ መሐመድ