1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእርስ በርስ ግጭትና ጦርነት የቀጠለባት የመን

ረቡዕ፣ መጋቢት 30 2007

በእርስ በርስ ግጭት የጦርነት ቀጣና የሆነችዉ የመን ይዞታ ወደሰብዓዊ ቀዉስ እያመራ መሆኑን የተመድ አመለከተ። የመንግሥታቱ ድርጅት የሕፃናት መርጃ UNICEF እንደገለፀዉ በጦርነቱ በሺዎች የሚቆጠሩት ከቤት ንብረታቸዉ ለመፈናቀል ሲዳረጉ፤ አጋጣሚዉ ለበሽታና ለምግብ እጥረት አጋልጧቸዋል።

https://p.dw.com/p/1F3H2
Jemen Humanitäre Lage
ምስል picture alliance/abaca

ስዑድ አረቢያ መራሹ የተባበረ ኃይል ሁቲ በመባል የሚታወቁትን የሺያት አማፅያንን በጦር ጀት መደብደብ ከጀመረ ከአስር ቀናት በላይ ተቆጥረዋል። በሁቲ አማፅያንና የፕሬዝደንት አቢድ ራቦ ማንሶር ሃዲ ደጋፊዎች መካከልም ባለፉት 24 ሰዓታት በደቡባዊት የመን ኤደን ከተማ የቀጠለዉ ዉጊያ ሲቪሎችን ጨምሮ ቢያንስ የ114 ሰዎችን ሕይወት መጥፋቱን ቀይ መስቀልን የጠቀሰዉ የፈረንሳይ የዜና ወኪል ዘገባ አመልክቷል። ሳዉዲ መራሹን ኃይል ለመደገፍ የተለያዩ ሃገራት ዝግጁነታቸዉን እየገለፁ ነዉ። ፓኪስታን ከሳዉዲ የጦር ጀቶችና መርከቦች እንዲሁም ወታደሮችን የማዋጣት ጥያቄ እንደቀረበላትና እንደምትተባበርም ገልጻለች። የእርስበርስ ግጭትና ጦርነት ስለቀጠለባት የመን የምሥራቅ አፍሪቃና የአካባቢዉን የፖለቲካ ተንታኝ ዩሱፍ ያሲንን ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሜ አንዳንድ ጥያቄዎች በማንሳት አነጋግሬያቸዋለሁ፤

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ