የእህል ምርት እና የእህል ዋጋ ይዞታ
እሑድ፣ የካቲት 24 2005ማስታወቂያ
እንደሚሰማው፡ ካለፈው ጥቅምት እስካለፈው ታህሳስ ወር ድረስ በነበረው ጊዜ ውስጥ የእህል ዋጋ በመጠኑ ቢቀንስም፡ ዋጋው አሁንም ውድ እንደሆን ነው የሚገኘው። ከጥር እስከ የካቲት ወር ደግሞ በእህል ዋጋ ላይ የታየው ጭማሪ የድሆቹንና የእጅግ ድሆቹን የመግዛት አቅም በጉልህ መቀነሱን አንዳንድ ጥናቶች አሳይተዋል። የአፋር እና የሶማልያ ክልሎች በመሳሰሉ አርብቶ አደሮች ያሉባቸው ምሥራቃዊ አካባቢዎች ውስጥ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጡ አዳጋች እንደሚሆንና ርዳታ እንደሚያስፈልግ የምርት አቅርቦት ትንበያ የሚያደርጉ ድርጅቶች አስታውቀዋል። የኢትዮጵያ የእህል ምርት ይዞታ እና የእህል ዋጋ በወቅቱ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል? የዚህ ሣምንት የውይይት ርዕስ አድርገነዋል።
አርያም ተክሌ
ልደት አበበ