የኤርትራውያን ስደተኞች ምስክርነት በኢጣልያ
ሐሙስ፣ ጥር 8 2006ማስታወቂያ
በህገ ወጥ መንገድ ሰዎችን በማዘዋወር በዝርፊያ ና አስገድዶ በመድፈር ክስ በተመሰረተበት ማህሙድ መሃመድ ተባለው የሶማሊያ ዜጋ በኢጣልያዋ የሲሲሊ ክፍለ ሃገር ዋና ከተማ ፓሌርሞ ፍርድ ቤት ተመሰከረበት ። ተከሳሹ በባህር ላይ ጉዞ ግፍ የፈፀመባቸው ኤርትራውያን በፓሌርሞው ፍርድ ቤት ቀርበው ባለፈው ሰኞ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል ። ለፍርድ ቤት ቃላቸውን የሰጡት 7 ኤርትራውያን ስደተኞች ናቸው ። ከመካከላቸው በተከሳሹ የተደፈረች የ18 ዓመት ልጃገረድ ትገኝበታለች ። ባለፈው ባለፈው ጥቅምት ወር በኢጣልያዋ ደሴት ላምፔዱዛ አቅራቢያ የተሳፈሩባት ጀልባ ሰጥማ ከሞቱት 366 ሰዎች መካከል በግለሰቡ የተደፈሩ ሴቶች ይገኙበታል ። ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስ ከሮም ዝርዝር ዘገባ አለው ።
ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሃመድ