የኤርትራና ኢትዮጵያ ስደተኞች ሰቆቃ
ረቡዕ፣ መጋቢት 25 2005እንዲከፍሉ ተወጥረው ይያዛሉ ። በየጊዜው ሰፋ ያሉ የሰቆቃ ዘገባዎች የሚደርሱት ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት AI በዛሬው ዕለትም በዚህ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥቷል። በድርጅቱ፤ የኢትዮጵያና ኤርትራ የሰብአዊ መብት ጉዳዮትች ተመራማሪ የሆኑት ክሌር ቤስተን--
በሱዳንና በግብፅ ፍዳ ስለሚያዩ ፣ ግፍ ስለሚፈጸምባቸው፣ በአሠቃቂ ሁኔታ ስለሚገደሉ ኤርትራውያንና ኢትዮጵውያን መከራ ፣ በየጊዜው ብዙ ይነገራል፤ ከምሥራቃዊው ሱዳን ሸጋረብ መጠለያ ጣቢያ AI ስለደረሰው ዘገባ ወ/ት ክሌር ቤስተን እንዲህ አብራርተዋል።
«ለ2 ዓመታት ያህል በምሥራቃዊው ሱዳን በሸጋረብ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ፣ የፖለቲካ ተገን ጠያቂዎችና ስደተኞች ታፍነው እንደሚወሰዱ፣ ተገደው ወደግብፅ እንዲሻገሩና ከዚያም ሲና በረሃ፣ ታግተው ፣ ከቤተሰቦቻቸው ማስለቀቂያ በዛ ያለ ገንዘብ እንዲከፍሉ እንደሚገደዱ መስማታችን አልቀረም ። ያገቷቸው ሰዎች ፍጹም ኢሰብአዊ የሆነ የግፍ ተግባር እንደሚፈጽሙባቸው፣
እንደሚደበደቡ፣ ናፍጣ በሰውነታቸው ላይ እየደፉ እንደሚያቃጥሏቸው፤ በኤሌክትሪክ ገመድ መግረፍና በሰቅጣጭ የኤሌክትሪክ ንዝረት እንደሚያሠቃዩአቸው፣ ሴቶችም ፣ ወንዶችም እንደሚደፈሩ፣ ከቤተሰብም ሆነ ቤተዘመድ ፤ ሰዎቹን ለማስለቀቅ፣ የሚጠየቀው ገንዘብም ከ 30 ሺ እስከ 40 ሺ የአሜሪካ ዶላር መሆኑን ከዘገባው ተገንዝበናል።»
አሁን ያወሱልን ዘግናኝ ድርጊት ባለፉት ዓመታትም፣ በተደጋጋሚ የተፈጸመ ነውና AI ም ሆነ ሌሎች መሰል ድርጅቶች፣ ይህ ሰቆቃ እንዲገታ ምን ያደርጋሉ?
« በዛሬው ዕለት ስለሁኔታው መግለጫ ሰጥተናል። በአንዳንድ እጅግ ዘግናኝ በሆኑ የሰብአዊ መብት ይዞታዎች ላይ ነው ማብራሪያ የሰጠነው። በመግለጫችንም ላይ በዛ ያሉ ሊፈጸሙ ይገባል ብለን ያሰብናቸውን ሐሳቦችና ማሳሳቢያዎች፤ ለሚመለከታቸው መንግሥታት አቅርበናል። ----»
ተክሌ የኋላ
አርያም ተክሌ