የኤሌክትሪክ ሞተር ብስክሌቶች
ረቡዕ፣ ግንቦት 14 2011ማስታወቂያ
በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠሩ መኪኖች የአከባቢ ብክልተን ለመቀነስና የገንዘብ ወጪን ለመቀነስ በእጅጉ እንደሚጠቅሙ አብዛኛዉ ዓለም የተስማማበት መስሏል።በተለይ በኢንዱስትሪ የበለፀጉ ሐገራት መንግሥታት የነዳጅ ፍጆታን ለማስወገድ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን የሚያመርቱ ኩባንዮቻቸዉን በገንዘብም ጭምር እየደጎሙ፣ተገልጋዩም አዲሱን ቴክኖሎጂ እንዲጠቀም እያበረታቱ ነዉ።ኢትዮጵያ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሠሩ መኪኖችን ማምረትም ሆነ መገጣጠም የምትችልበት ደረጃ ላይ አልደረሰችም።ይሁንና አዲስ አበባ የሚገኝ አንድ ኩባንያ በኤልክትሪክ ኃይል በሚሞሉ ባትሪዎች የሚሽከረከሩ ሞተር ብስክሌቶችን እየገጣጠመ ለገበያ እያቀረበ ነዉ።የሞተር ብስክሌቶቹ ዓይነት፤የኃይል አጠቃቀማቸዉ፤ በተገልጋዩ ዘንድ ያላቸዉ ተፈላጊነትና አምራቾቹ የገጠማቸዉ ፈተና የዛሬዉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዝግጅታችን ትኩረት ነዉ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
ተስፋአለም ወልደየስ