የኢጣልያ ምርጫ
ሰኞ፣ የካቲት 18 2005ማስታወቂያ
ከጥቂት ሰዓታት በፊት የተጠናቀቀው የኢጣልያ ምርጫ ውጤት አጓጓ ሆኗል ። የምርጫ
ጣቢያዎች ከተዘጉ በኋላ የወጡ ዘገባዎች የፕየር ሉጂ ቤራሳኒ የመሃል ግራ ጥምረት
የአወዛጋቢውን የሲልቭዮ ቤርሉስኮኒን የመሃል ቀኝ ፓርቲ እየመራ መሆኑን
ይጠቁማሉ ። ይሁንና የሮም ኤጣልያው ዘጋቢያችን ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስ ለኢጣልያ
630 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎችና ለ 315 የህግ መወሰኛ ምክር ቤት
መቀመጫዎች የተካሄደው ምርጫ ውጤት ይህ ሊሆን ይችላል ብሎ ከወዲሁ ለመገመት
አስቸጋሪ ነው ይላል ። ተክለ እዝጊን ስቱድዮ ከመግባቴ በፊት በስልክ አነጋግሬው ነበር ።
ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስ
ሂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ