የኢድ አል አድሀ አከባበር በአዲስ አበባ ስታድዮም
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 15 2010ማስታወቂያ
ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ሙስሊሞች ዛሬ የኢድ አል አድሀ አረፋ በዓል እየተከበረ ነው። በዓሉ በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ ስታድዮም በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በስግደት እና የፀሎት ስነስርዓት ዛሬ ጠዋት ተከብሯል። በበዓሉ ላይ የተገኙት የሃይማኖት መሪዎች እና የከተማዋ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በስነ ስርዓቱ ላይ ባሰሙት ንግግር የሰላም የአንድነት እና የመረዳዳት መልዕክቶች እና ጥሪዎችን አስተላልፈዋል። ስነ ስርዓቱን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ