የኢትጵያ አካባቢያዊ ምርጫና ተቃዋሚ ፓርቲዎች
ማክሰኞ፣ ጥር 7 2005ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥትን የሚቃወሙ ሠላሳ-ሰወስት የፖለቲካ ማሕበራት በመጪዉ ሚያዚያ በሚደረገዉ አካባቢያዊና የአዲስ አበባ መስተዳድር ምርጫ እንደማይሳተፉ አስታወቁ።የሰላሳ-ሰወስቱ ፓርቲዎች ጊዚያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ዛሬ እንዳስታወቀዉ ምርጫዉ ሠላማዊ፥ ነፃና ፍትሐዊ እንዲሆን እና ከመንግሥትና ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር ለመወያየት ፓርቲዎቹ በተደጋጋሚ ያቀረቡት ጥያቄ ዉድቅ ሥለሆነባቸዉ እራሳቸዉን ከምርጫዉ ለማግለል ተገድደዋል።ፓርቲዎቹ አቋማቸዉን ለሕዝብ ለማስረዳት በቅርቡ አዲስ አበባ ዉስጥ የአዳራሽና የአደባባይ ሕዝባዊ ሥብሰባ እንደሚጠሩም አስታዉቀዋል።ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የጊዚያዊ ኮሚቴዉን ሊቀመንበር አነጋግሮ የሚከተለዉን ዘገባ ልኮልናል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ