የኢትዮ አይሁዶች ተሳትፎ በእስራኤል ምርጫ
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 17 2005ማስታወቂያ
የፊታችን ጥር አጋማሽ የእስራኤል ምክር ቤት ማለትም የክኔሴት ምርጫ ይካሄዳል ። በዚህ ምርጫም በርካታ ኢትዮጵያውያን አይሁዶች ይወዳደራሉ ። ከመካከላቸውም የትላልቆቹ የሊኪድ የካዲማና የመሳሰሉት ፓርቲዎች እጩዎች ሲገኙበት ኢትዮጵያውያን አይሁድ ፖለቲከኞች የመሰረቱት አንድ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲም በምርጫው ይሳተፋል ። „ወንድማማቾች ነን „ የተሰኘው የዚህ ፓርቲ አላማ የኢትዮጵያውያን አይሁዶችን ጥቅም ማስጠበቅ መሆኑን የፓርቲው መሪዎች አስታውቀዋል ። የእስራኤል ሃይፋው ወኪላችን ግርማው አሻግሬ እንደዘገበው እስራኤል ካሉት 136 ሺህ ኢትዮጵያውያን አይሁዶች 84 ሺ ያህሉ የመምረጥ መብት አላቸው ። ግርማው በጥሩ የእስራኤል ፓርላማ ምርጫ የኢትዮጵያውያን አይሁዶችን ተሳትፎ በቀጣዩን ዘገባው ቃኝቶታል ።
ግርማው አሻግሬ
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ