የኢትዮ-አሜሪካዊው ይግባኝ
ሐሙስ፣ ኅዳር 1 2009ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥት ሰላይ ሶፍትዌር በመጠቀም በኢሜል እና በተለያዩ ሶፍትዌሮች አማካይነት የሚደርሷቸውን እና የሚልኳቸውን መረጃዎች ሲበረብር ነበር ያሉ አንድ ኢትዮጵያዊ -አሜሪካዊ መንግሥትን ኢዚያው አሜሪካን ከሰው ክሱ ቢዘጋም ይግባኝ ማለታቸው ተዘግቧል ። እኚሁ ኪዳኔ የሚባሉ ሰው የኢትዮጵያ መንግሥት የግል የኢሜል ልውውጦችን በስልክ በስካይፕ እና በሌሎችም ሶፍትዌሮች የሚያስተላልፏቸውን እና የሚቀበሉዋቸውን መልዕክቶች ጠልፎብኛል ሲሉ ከሁለት አመት በፊት ነበር ለመጀመሪያ የአሜሪካን የፌደራል ፍርድ ቤት ክሱን ያቀረቡት ። ፍርድ ቤቱም የኢትዮጵያ መንግሥት ጠበቆች አቁሞ ሲከራከር የቆየበትን ጉዳይ የማየት ሥልጣን እንደሌለው ገልጾ ክሱን ዘግቶት ነበር ። ሆኖም ግለሰቡ ብይኑን በመቃወም በቅርቡ ዋሽንግተን ዲሲ ለሚገኝ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ይግባኝ አቅርበዋል ። ዝርዝሩን መክብብ ሸዋ አዘጋጅቶታል ።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ