የኢትዮ ቴሌኮም ሽልማትና ስሞታዉ
ሰኞ፣ ጥቅምት 15 2008ማስታወቂያ
በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ የስልክ አገልግሎት ተጠቃሚዎች ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት፤ ኢትዮ ቴሌኮም ለደንበኞቹ የሚሰጠዉ አገልግሎት ደካማ ሆኖ ሳለ የጥራት ተሸላሚ መባሉ ግራ የሚያጋባ ነዉ ። ኢትዮ ቴሌኮም በበኩሉ ሽልማቱ የአስተዳደር ጥራት መሆኑንና ደንበኞች ለአቀረቡት አቤቱታ ተገቢዉን ምላሽ ለመስጠት ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑን መግለጹን ፤ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሄር በላከልን ዘገባ ያሳያል።
ዮሐኃንስ ገ/እግዚአብሄር
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ