የኢትዮጽያ የወራት ስያሜና ፍችዉ
ሐሙስ፣ ኅዳር 2 2003ማስታወቂያ
የጥቅምት ማር በመድህኒትነቱ ታዋቂ በመሆኑ፣ በጥቅምት ጎተራዉም ስለሚጎድል መቆጠብ እንዳለበት ለመግለጽ። ስለጥቅምት ብዙ ይባላል፣ ዛሪ ህዳር ከባተ በሁለተኛ ቀኑ ደግሞ በህዳር እሸት ሁሉ ዳር ዳር ብለናል! የአስራ ሶስት ወር ጸጋ ኢትዮጽያችን ከርዕሰ አዉደ አመት ከመስከረም ጀምሮ እስከ አስራ ሶስተኛ ወር ጳግሜ ድረስ ወራቱ የተለያዩ መጠሪያዎች አባባሎች ስነ-ቃሎች እናገኛለን! የሚገርመዉ ደግሞ የኢትዮጽያ የወራት ስያሜ ከግብርና ህይወት ከእርሻ ጋር የተያያዘ መሆኑ ነዉ። በለቱ ዝግጅታችን ስለ ኢትዮጽያ የወራት ስያሜ እና ከወራቶች ጋር ስለሚባሉ ስነ-ቃሎች እና ወቅቶች ባለሞያ ጠይቀን ልናካፍል ይዘናል ያድምጡ!
አዜብ ታደሰ
ሂሩት መለሰ