የኢትዮጽያ ምሁራኖች በፊደራሊዝምና ዲሞክራሲ ላይ ያደረጉት ዉይይት
ሐሙስ፣ መጋቢት 16 2002ማስታወቂያ
ፊደራሊዝምና ዲሞክራሲ በኢትዮጽያ በሚል በሂልተን ሆቴል በቀረበዉ ጥናት ላይ ምሁራኑ የሞቀ ክርክር ማድረጋቸዉ ተገልጾአል። ጥናቱን እና ዉይይቱን በገንዘብ ድጋፍ ያደረገዉ የጀርመኑ Friedrich-Ebert-Stiftung በመባል የሚታወቀዉ ድርጅት ነበር። በቅርቡ በአለም አቀፍ የግጭቶች አስወጋጅ ድርጅት ICGየተሰራ ጥናት እንዳስታወቀዉ በኢትዮጽያ እየተገበረ ያለዉ ጎሳና ቋንቋን መሰረት ያደረገዉ ፊደራላዊ ስርአት ለግጭቶች መባባስ ምክንያት እንደሆነ ማስታወቁ የሚታወስ ነዉ ዝርዝሩን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ልኮልናል።
ታደሰ እንግዳዉ፣ አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ