1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጽያዉያን ማህበር በሙኒክ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 17 2000

የኢትዮጽያ የባህል ማህበር በተሰኘ እዚህ በጀርመን በባቫርያ ግዛት በሙንሽን ከተማ እና አካባቢዋ የሚገኙ ኢትዮጽያዉያን ያቋቋሙት ባህላዊ ማህበር ዘንድሮ ለሁለተኛ ግዜ የኢትዮጽያን ታሪክ የሚያሳይ፣ ባህልን የሚገልጽ ደማቅ በአል አዘጋጅቶ ነበር።

https://p.dw.com/p/EPsN

በዚህ ደማቅ ባህልን የማስተዋወቅ ስነ-ስርአት ላይ የወንጌላዊት ግሪክ ቤተክርስትያን ባልደረቦች፣ የከተማዉ የዉጭ ጉዳይ መስርያ ቤት ተጠሪዎች፣ ሰዎች ለሰዎች ማለት ሜንሽን ፎር ሜንሽን መንግስታዊ ያልሆነ የርዳታ ድርጅት መስራቤት ሰራተኞች እንዲሁም ልዑል አስፋዉ ወሰን አስራቴ ተገኝተዋል፣ ስለ በአሉ አከባበር ስለ ማህበሩ ያነጋገርናቸዉ ኢትዮጽያዉያን የዛሪዉ የባህል መድረካችን እንግዶች ናቸዉ መልካም ቆይታ