የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ቀዉስ መነሻዉና መፍትሔዉ
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 11 2010ማስታወቂያ
የመቀሌዉ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ መምሕርና የሥልታዊ ጥናት ማዕከል ኃላፊ አቶ መረሳ ፀኃዬ «ኢትዮጵያ አደገኛ ሁኔታ ዉስጥ ነች» ይላሉ። ሐገሪቱን የሚብጠዉ ተቃዉሞ፤ግጭት፤ ግድያና መፈናቀል ምክንያት ደግሞ ከተቃዉሞዉ እኩል በኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች ወይም መሪዎች መካከል «የዓላማ አንድነት» አለመኖሩ ነዉ ባይ ናቸዉ።መፍትሔዉም ኢሕአዴግ አንድነቱን አጠንክሮ ሲቆም የሚገኝ ነዉ-እንደ አቶ መረሳ እምነት።ይሁንና ኢትዮጵያ ከእንግዲሕ እስካሁን በተጓዘችበት መንገድ መቀጠልዋን የፖለቲካ ተንታኙ ይጠራጠራሉ።እንዴት? በስልክ አነጋግሬያቸዋለሁ።
ነጋሽ መሐመድ
ሸዋዬ ለገሰ