1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ጦር እና አሚሶም

ረቡዕ፣ ጥር 14 2006

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት አሁን ጦሩ በአሚሶም ዕዝ ሥር የተጠቃለለዉ በጋራ መንቀሳቀሱ የጦሩን ተዕልኮ ከግብ ለማድረስ ጠቃሚ በመሆኑ ነዉ።የወጪ ጉዳይም ከግምት የሚገባ ነዉ።አሚሶምን የተቀየጠዉ የኢትዮጵያ ጦር አራት ሺሕ ወታደሮች አሉት ።

https://p.dw.com/p/1AvTb
የኢትዮጵያ ጦር እና አሚሶም
ምስል Getachew Tedla

ሶማሊያ የሠፈረዉ የኢትዮጵያ ጦር እዚያዉ በሠፈረዉ የአፍሪቃ ሕብረት ሠራዊት (AMISOM) ዕዝ ሥር ዛሬ በይፋ ተጠቃለለ።ኢትዮጵያ የሶማሊያዉን አክራሪ ደፈጣ ተዋጊ ቡድንን አሸባብን እንዲወጋ ከሁለት ሺሕ ሰወስት ጀምሮ ዳግም ሶማሊያ ዉስጥ ያሰፈረችዉ ጦር እስከ ዛሬ በራሱ ወጪ፥ ዕዝ እና መዋቅር ሲንቀሳቀስ ነበር።የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣናት እንዳስታወቁት አሁን ጦሩ በአሚሶም ዕዝ ሥር የተጠቃለለዉ በጋራ መንቀሳቀሱ የጦሩን ተዕልኮ ከግብ ለማድረስ ጠቃሚ በመሆኑ ነዉ።የወጪ ጉዳይም ከግምት የሚገባ ነዉ።አሚሶምን የተቀየጠዉ የኢትዮጵያ ጦር አራት ሺሕ ወታደሮች አሉት።ሥለ እርምጃዉ የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲን በስልክ አነጋግሬቸዋለሁ።

ነጋሽ መሐመድ

ሒሩት መለሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ