የኢትዮጵያ-ጀርመን የምርምር እና የባህል ልዉዉጥ
ሐሙስ፣ መስከረም 22 2007ማስታወቂያ
የብራና መጻሕፍት የቋንቋ የባህል የታሪክ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ምርምርና ጥናት ስራቸዉ ይታወቃል። ይህ የምርምርና የባህል ልዉዉጥ የበለጠ እንዲልቅ በማሰብ ከጥቂት ዓመታት በፊት ጥናቱ በሁለቱም ሀገራት ላይ እንዲቀጥል የሀንቡርግ የባሕር ዳር እንዲሁም ደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲዎች የምርምር ስራዎቻቸዉን ለመለዋወጥ እና ተማሪዎች በሁለቱም ሀገራት ልምዶችን እንዲቀያየሩ ለማስቻል «ዓባይ የጥናት የምርምር ማዕከል» በሚል ባህር ዳር ዩንቨርስቲ ላይ ማዕከል ተቋቁማል። በለቱ ዝግጅታችን የዚህ ማዕከል መስራች በሐንቡርግ ዩንቨርስቲ ዶክተር ጌቴ ገላዩ እንዲሁም ሰሞኑን ለሥራ ጉብኝት ወደ ጀርመን በርሊን የመጡት በባህር ዳር ዩንቨርስቲ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ተስፋዬ ሽፈራዉን የለቱ ዝግጅታችን እንግዶች አድርገናል።