የኢትዮጵያ የፖለቲካ ቀውስ እና መፍትሔው
ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 24 2010ማስታወቂያ
ለጋዜጠኛው ለማርቲን ፕላውት ነገሩ ግልጽ ነው፡፡ እርሱ እንዳለው አሁን በኢትዮጵያ የሚታየው የተቃውሞ እንቅስቃሴ የችግሩቹ ሁሉ መነሻ ተቋጥረው የተቀመጡበት ነው፡፡ “የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ድርጅት እና አቶ መለስ ዜናዊ የዲሞክራሲ ስርዓት እና እውነተኛ ፌደራሊዝምን በሀገሪቱ በኢትዮጵያ ለመዘርጋት ፍላጎት አልነበራቸውም፡፡ አላማቸውም አይደለም፡፡ በህገመንግስቱ አንቀጽም ላይ እንደሚታየው እነሱ ያተኮሩት በብሔር ልዩነት እና በብሔር ክፍፍሉ ላይ ነበር፡፡ በብሔር ልዩነት ላይ አተኩሮ አንድ ሀገር እና አንድ መንግስት ለመመስረት የሚጥር ኃይል ደግሞ በመጨረሻ እርሱ የሚያጭደው የብሔር ጥላቻ እና በብሔር ላይ የተመሰረተ ግጭቶችን ነው ” ብለዋል ፕላውት፡፡
የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ጉዳዮችን በቅርበት የሚከታተሉት ጋዜጠኛ ማርቲን ፕላውት “የሆነው ይሁን ኢትዮጵያ ተፈረካክሳ እና ተበታትና ከዓለም ካርታ ላይ አትጠፋም” ሲሉ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ እንደጋዜጠኛው ሁሉ ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስም “ኢትዮጵያ በምንም ዓይነት ተፈረካክሳ አትወድቅም” ባይ ናቸው፡፡ የበርሊኑ ዘጋቢያችን ይልማ ኃይለሚካኤል ያጠናቀረውን ሙሉ ዘገባ የድምጽ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ፡፡
ያን ፊሊፕ ቬልሄል/ ይልማ ኃይለሚካኤል
ሸዋዬ ለገሠ