የኢትዮጵያ የዱር እንስሳ ጥበቃ
ሐሙስ፣ የካቲት 9 2009ማስታወቂያ
ኢትዮጵያና ሲንጋፑር የዱር እንስሳና ዉጤቶቻቸዉን ሕገ ወጥ ዝዉዉር በጋራ ለመቆጣጠር ያስችላል ያሉትን ስምምነት በቅርቡ ተፈራርመዋል።በቅርቡ ሲንጋፑርን የጎበኘዉ የኢትዮጵያ የባለስልጣኞች ጓድ እንደሚለዉ ሥምምነቱ ለኢትዮጵያ የዱር እንስሳት የሚደረገዉን ጥበቃና ክትትል ለማሻሻልና ለማጠናከር ጠቃሚ ነዉ።ትላልቅ ወደቦች ያሏት ትንሺቱ እስያዊት የከተማ ሐገር ሲንጋፑር ከፍተኛ መጠን ያለዉ የዱር እንስሳ ዉጤት ይዘዋወርባታል።የደቡብ አፍሪቃዉ ወኪላችን መላኩ አየለ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
መላኩ አየለ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ