የኢትዮጵያ የአምስት ዓመት የልማት ዕቅድ6 መስከረም 2003ሐሙስ፣ መስከረም 6 2003የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ መንግስታቸው በመጪዎቹ አምስት ዓመታት የአስራ አምስት በመቶ ዕድገት ለማስመዝገብ ማቀዱን አስታውቀዋል ። በዚህ ጊዜ ውስጥም አገሪቱ ያለ ውጭ ዕርዳታ ህዝቧን ለመመገብ ዕቅድ ማውጣቷንም አቶ መለስ ተናግረዋል ።https://p.dw.com/p/PDsPምስል picture alliance/dpaማስታወቂያ ይሁንና ኢትዮጵያ በመጪዎቹ አምስት ዓመታት አስመዘግባለሁ ያለችው ይህ የኢኮኖሚ ዕድገት ሊሳካ መቻሉ የአፍሪቃ ቀንድ የኢኮኖሚ ጉዳዮች ተንታኝ ክርስቶፈር ኢድስ ለዶይቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ እንደተናገሩት አጠራጣሪ ነው ። በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናንን ለማረጋገጥም እንደተንታኙ አንዳንድ መርሆች ማስተካከል ይገባቸዋል ። ሂሩት መለሰ ነጋሽ መሐመድ