የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች መርኀ-ግብር
ረቡዕ፣ የካቲት 27 2005ማስታወቂያ
ከአዲስ አበባ ፣ ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር የላከልን ዘገባ እንደሚያስረዳው፤ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች መርኀ ግብር፤ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ከመጽደቁ በፊት፤ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ጋር ትናንት ውይይት ተደርጎበታል። ረቂቁ ቀደም ሲል በሚንስትሮች ም/ቤት መጽደቁ ተነግሯል። የትናንቱ ውይይት ዓላማ፤ ሰነዱ፤ ለተወካዮች ም/ቤት ቀርቦ ከመጽደቁ በፊት፣ ከባለድርሻ አካላት የሚገኘው ጠቃሚ ሐሳብ፤ ግብዓት ሆኖ እንዲያገለግል ታስቦ ነው ተብሏል።
በውይይቱ፣ የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ፣ የኢትዮጵያን ተወካይ ጨምሮ፣አምባሳደሮችና የተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ተወካዮች ተገኝተዋል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ተክሌ የኋላ
ሸዋዬ ለገሠ