የኢትዮጵያ የመንጃ ፍቃድ ሕግና ቅሬታዉ
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 4 2004ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥት በቅርቡ የደነገገዉ የመንጃ ፍቃድ የትምሕርና የሥልጠና ደንብ ከባለ ጉዳዮች ድጋፍም ተቃዉሞም ገጥሞታል።አንዳዶች እንደሚሉት የመንጃ ፍቃድ ትምሕርት፥ ሥልጣናና ፍቃዱ ከመንግሥት እጅ ወጥቶ በግል ኩባንዮች መያዙ የአሰራሩን ሒደት አቀላጥፎታል።ሌሎች ግን ሒደቱ የመቀላጠፉን ያክል ለትምሕርቱና ፍቃዱን ለማግኘት የሚከፈለዉ የገንዘብ መጠን የማይነካ ነዉ ባዮች ናቸዉ።እንደገና ሌሎች «ቀልጣፋ» የሚባለዉ መንጃ ፍቃድ የማዉጣቱ ሒደት ሕይወትና ንብረትን ላደጋ ያጋልጣል ባይ ናቸዉ።የድሬዳዋ መንገድ ትራንስፖርት ቅርንጫፍ ሐላፊ አቶ መሐመድ አሕመድ ሥለ ዋጋዉ ዉድነት የሚቀርበዉን ሥሞታ ትክክል ሲሉት፥ ሥለአደጋዉ ግን መጣራት አለበት ይላሉ።ዩሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ዝርዝር ዘገባ አለዉ።
ዮሀንስ ገብረ እግዚያብሄር
ነጋሽ መሐመድ
ተክሌ የኋላ