የኢትዮጵያ እና አሜሪካ ግንኙነት
ሐሙስ፣ ሚያዝያ 4 2010ማስታወቂያ
የዩናይትድ ስቴትስ ሕግ መምሪያ ምክር ቤት የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ይዞታ እንዲሻሻል የሚጠይቀዉን ረቂቅ ዉሳኔ ማፅደቁን የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር በድጋሚ ነቀፈዉ።የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም በሳምታዊ ጋዜጣዊ መግለጫቸዉ ዛሬ እንዳሉት የአሜሪካ ምክር ቤት ያፀደቀዉ ሠነድ ከተቀመጠበት መደርደሪያ ሊንቀሳቀስ አይችልም።ቃል አቀባዩ ኢትዮጵያ በፅጥታዉ ምክር ቤት ዉስጥ ሥላላት ተሳትፎ እና ከጎረቤቶችዋ ሐገራት ጋር ሥላላት ግንኙነትም ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጋዜጣዊ መግለጫዉን ተከታትሎታል።
ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ