የኢትዮጵያ ወታደሮች በሶማሊያ መቆየት
ሰኞ፣ ሰኔ 18 2004ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ በህዳር ወር ነበር ታንኮች እና በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን ወደ ሶማሊያ የላከችው። የተልዕኮው አላማ በሶማሊያ የሚገኘውን አማፂ ቡድን አሸባብን በመውጋት በአጭር ጊዜ ውስጥ ሶማሊያን ለቆ እንዲወጣ ለማድረግ ነበር። ይሁንና ሮይተርስ የዜና ወኪል ያለፈው ቅዳሜ ባወጣው ዘገባ፤ ኢትዮጵያ ወታደሮቿን የአፍሪቃ ህብረት እንዳለው በሚያዚያ ወር መጨረሻ ሳይሆን በሰኔ ወርም አላስወጣችም። እንደውም ተልዕኮዋቸው እንደሚራዘም አመልክታለች። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ኢትዮጵያ ወታደሮቿን በሶማሊያ የምታቆይበትን ምክንያት ለዶይቸ ቬለ ገልፀዋል።
ልደት አበበ
ተክሌ የኋላ