የኢትዮጵያ ኤኮኖሚ ይዞታና የውጭ ምንዛሪ እጥረት
እሑድ፣ ሚያዝያ 28 2010ማስታወቂያ
የውጭ ንግድ እንደሚፈለገው አለማደጉ፣ በሀገር ውስጥ ቁጠባ እና በኢንቬስትመንት መካከል ያለው ልዩነት ግልጽ አለመሆኑን፣ ከሁሉም በላይ ግን የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንደ ዋነኛ ችግር ይጠቀሳሉ። አዲሱ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶክተር አብይ አህመድ በሀገሪቱ በተለይ ባለፉት ሶስት ዓመታት ለታየው የፖለቲካ ቀውስ መፍትሔ በማስገኘት በቀውሱ ሰበብ ችግር የገጠመው የምጣኔ ሀብት ይዞታ የሚሻሻልበትን ዘዴ ያስገኙ ይሆናል በሚል ብዙዎች ተስፋ አድርገዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ ባጠቃላይ ኤኮኖሚውን ለማነቃቃት እስካሁን የጠቆሙት የፖሊሲ አቅጣጫም ግን የለም። የሳምንቱ ውይይታችን በኢትዮጵያ ኤኮኖሚ ይዞታ እና በተለይ በውጭ ምንዛሪ እጥረት ላይ አትኩሯል።
ሙሉ ውይይቱከታች የድምፅ ማዕቀፉ ውስጥ ይገኛል።
አርያም ተክሌ
ማንተጋፍት ስለሺ