የኢትዮጵያ አይሁዳውያን መታሰቢያ በእሥራኤል
ረቡዕ፣ ግንቦት 27 2006ማስታወቂያ
ለሟቾቹ መታሰቢያ እንዲሰራ ሰፊ ድርሻ ያበረከተው የቤተ እሥራኤላውያኑ ድርጅት ይኸው ርምጃ እንዳስደሰተው ቢገልጽም፣ የሁሉም ሟቾች ስም በሐውልት ላይ ባለመቀረጹ ቅር መሰኘታቸውን አስታውቀዋል። በዚሁ ጉዞ ሕይወታቸው የጠፋው ሰዎች ቁጥር 4,000 እንደሚሆን በጉዳዩ ላይ ጥናት ያደረጉ ጠበብት ይገምታሉ። የእሥራኤል ፕሬዚደንት ሺሞን ፔሬስ፣ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ፣ እንዲሁም፣ ከፍተኛ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት እና የምክር ቤት አባላት ስለተገኙበት ስለዚሁ ልዩ ሥነ ሥርዓት የሀይፋ ወኪላችን ግርማው አሻግሬ የድርጅቱን ፕሬዚደንት አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
ግርማው አሻግሬ
አርያም ተክሌ
ነጋሽ መሐመድ