የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሥራና እቅድ
ረቡዕ፣ ጥቅምት 20 2006ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ አየር መንገድ ባለፉት ሰባት ዓመታት የላቀ እድገት ለማስመዝገብ መብቃቱን የአየር መንገዱ ሃላፊ አስታወቁ ። አየር መንገዱ ወደ ፍራንክፈርት ጀርመን በረራ የጀመረበትን 55 ተኛ ዓመት ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ ፍራንክፈርት ውስጥ ባሰበበት ወቅት የድርጅቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ድርጅታቸው 2025 በተሰኘው እቅዱ በርካታ ውጥኖቹን ተግባራዊ አድርጓል፤ የተቀሩትንም ከግብ ለማድረስ እየጣረ ነው ። በካርጎ አገልግሎት መዘግየትና መንገደኞችን በማስተጓጓል አየር መንገዱ ስለ ሚቀርብበት ወቀሳ ዶቼቬለ የጠየቃቸው የፍራንክፈርት የስራ ሃላፊ ችግሮቹን ለማስወገድ የመፍትሄ እርምጃዎች እንደሚወሰዱ አስታውቀዋል ። በፍራንክፈርቱ ስነስርዓት ላይ የተገኘው የወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ዝርዝሩን ያቀርብልናል ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ