የኢትዮጵያ አሕዮች ጤና፥ አገልግሎትና ዋጋቸዉ
ማክሰኞ፣ ኅዳር 8 2002ማስታወቂያ
የፕሮፌሰሩ ከራቫት-የድሬዳዋዉ ወኪላችን ዩሐንስ ገብረ እግዚ አብሔር እንዳየዉ በአሕያ ምሥል ያጌጤ ነዉ።ያጠኑት፥የሚሠሩትም ሥለ አሕያና ለአሕያ-ነዉ።አሕያ ለኢትዮጵያዊዉ የሚሰጠዉ አገልግሎት እጅግ ነዉ።ያገልግሎት ዋጋዉ ግን ዱላ።ምሳሌ-አብነትነቱም ስንፍና ደደብነት ነዉ።የለምንነቱ ጥያቄ መልስ በርግጥ ብዙ ያጣቅሳል።ብዛቱ ግን-እስከ አምስት ሚሊዮን ይደርሳል።አይነት፥መልኩ አብሲኒያ፥ ስናር፥ ጅማና ኦጋዴን በሚል ስም ባራት ይከፈላል።ጤንነቱ ደግሞ-ፕሬፌሰሩ ይነግሩናል።
ዩሐንስ ገ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
ሒሩት መለሰ