የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መግለጫ
ሐሙስ፣ ግንቦት 27 2007ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተራዘመው የቦንጋ ምርጫ ሰኔ 7 ፣ 2007 ዓም እንደሚካሄድ አስታወቀ ። የቦርዱ ሃላፊዎች ዛሬ በሰጡት መግለጫ የዚህ ምርጫ ሪፖርትም ሰኔ 15 ቀን ይፋ በሚደረገው አጠቃላይ ዘገባ ውስጥ ተካቶ እንደሚቀርብ ተናግረዋል ። ከዚህ ሌላ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫውን ውጤት አንቀበልም ማለታቸው አሳፋሪ ነው ሲሉ ሃላፊዎቹ በመግለጫቸው አስታውቀዋል ። ከምርጫው በፊት ለቦርዱ የቀረቡ ቅሪታዎች እልባት ማግኘታቸውን የተናገሩት ሃላፊዎቹ በምርጫው ቀን ግን ለቦርዱ የቀረበ ቅሬታ እንደሌለም ገልፀዋል ። ጋዜጣዊ መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚዘብሔር ዝርዝር ዘገባ አለው ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚ እግዚዘብሔር
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ