የኢትዮጵያ ቡና አምራቾችን ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለው እቅድ
ረቡዕ፣ መስከረም 5 2014ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ቡና አምራች አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ያደርጋል የተባለለት ዕቅድን ለማስተግበር ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ውይይት ተካሄደ። «ቤኔፊት ኮርፖሬሽን ፎር አፍሪካ» የተሰኘውና ምስረታውን አሜሪካ ሜሪላንድ ግዛት ያደረገው የቡናን ግብዓት ለመላክ የሚንቀሳቀሰው ቡድን ዛሬ ውይይቱን አካኺዷል። አሜሪካ ኗሪ በኾሆኑ ኢትዮጵያውያን አባላት ቀስቃሽነት የተመሰረተው ይህ ቡድን አድማሱን ወደ አፍሪቃ ለማስፋትም እየሠራ ነው ተብሏል። የኢትዮጵያ የዘርፉ ባለስልጣናትንም ዛሬ ያሳተፈው የውይይት መድረክ የመግባቢያ ሰነድን በመፈራረም ኢትዮጵያ ከዘርፉ የምታገኘውን ተጠቃሚነት እንድታሳድግ ይረዳልም ተብሏል።
ሥዩም ጌቱ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ