የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ
ሰኞ፣ ሚያዝያ 21 2005ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ ውስጥ በሳይንስ መስክ ለሚካሄዱ ጥናትና ምርምሮች የሚሰጠው ድጋፍ አለመጠናከር በመስኩ ለሚደረጉ እንቅስቃሴዎች እንቅፋት መሆኑን የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ አስታወቀ ። የአካዳሚው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ደምሴ ሃብቴ ደምሴ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት በኢትዮጵያ የምርምር ሥራዎችን በሰፊው የሚደግፍ የተጠናከረ አካል የለም ። ሆኖም በቅርቡ ይመሠረታል ተብሎ የሚጠበቀው የኢትዮጵያ የጥናትና ምርምር ምክር ቤት በኢትዮጵያ ለሳይንስ ጥናትና ምርምር የሚሰጠውን ድጋፍ ያጠናክራል የሚል ተስፋ ተጥሎበታል ። ያነጋገራቸው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል ።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ