1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ መንግስት፣ የግንቦት ሰባት መሪዎች ጉዳይና አምነስቲ ኢንተርናሽናል

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 29 2001

ነዋሪነታቸው በአውሮጳና በአሜሪካ የሆኑና በቅርቡ በኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት፡ እንዲሁም፡ በሀገሪቱ የልማት ተቋማት ላይ የተቀነባበረ የሽብር ጥቃት ለመጣል አቅደው ሲንቀሳቀሱ ሴራቸው ከሽፎዋል ሲል መንግስት ቀደም ሲል መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል።

https://p.dw.com/p/HlQQ
የአምነስቲ ኢንተርናሽናል አርማ

የዚሁ ዕቅድ ተሳታፊ ናቸው ያላቸውን ከፍተኛ የሰራዊቱን መኮንኖችና ሲቭል ሰራተኞችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያካሄደ መሆኑንም የኮሚውኒኬሽን ጉዳዮች ሚንስትር ዴታ አቶ ኤርሚያስ ለገሰ ዛሬ በተለይ ለዶይቸ ቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ ገልጸዋል።ይህንኑጉዳይ በተመለከተ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የኢትዮጵያ መንግስት ከአንድ ሳምንት ገደማ በፊት ያሰራቸውን የሰላሳ አምስት እስረኞችን ስም እንዲገልጽ ትናንት ጠይቆዋል።የድርጅቱ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ ሚሼል ካጋሪ ለዶይቸ ቬለ እንዳስታወቁት፡ ከታሰሩት መካከል እስካሁን የሁለቱ ግለሰቦች ማንነት ብቻ ነው የተገለጸው። የአምነስቲን መግለጫ ሚንስትር ዴታው፣ ድርጅቱ በምርመራውና በፍርድ አያያዝ ጉዳይ ላይ ጫና ለማሳረፍና ህግ እንዳይተረጎም ለማድረግ ያደረገው ነው ብለውታል።

ድልነሳ ጌታነህ/ታደሰ እንግዳው/አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሐመድ