የኢትዮጵያ መንግሥት መርሕ ና አዲሱ ዓመት
ረቡዕ፣ መስከረም 2 2005ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግሥት ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ባገባደደዉ አዲስ ዓመት ዋዜማ ከአንድ ሺሕ ዘጠኝ መቶ በላይ እስረኞችን በይቅርታ ለቅቋል።መንግሥት ከዚሕም በተጨማሪ የሐገሪቱ ምክር ቤት ሐቻምና ባሸባሪነት ከፈረጃቸዉ ሠወስት የሐገር ዉስጥ የፖለቲካ ድርጅቶች መካካል ከኦጋዴን ብሔራዊ ነፃ አዉጪ ግንባር (ኦብነግ) ለመደራደርም ተስማምቷል።ናይሮቢ-ኬንያ ዉስጥ በስማበለዉ ይደረጋል የተባለዉ ድርድር ሒደት እስካሁን ግልፅ አይደለም።ይሁንና ድርድሩ ከእስረኞቹ መለቀቅ ጋር ተዳምሮ የኢትዮጵያ መንግሥት በተቃዋሚዎቹ ላይ የያዘዉን አክራሪ አቋም የማለሳለሱ ምልክት ነዉ-አይደለም የሚል ክርክር ማስነሳቱ አልቀርም።ገመቹ በቀለ በዚሕ ጉዳይ ላይ ሁለት የፖለቲካ ተንታኞችን አነጋግሮ ያጠናቀረዉ ዘገባ አለ።
ገመቹ በቀለ
ሒሩት መለሰ