የኢትዮጵያ ልዑካን በጀርመን
ሰኞ፣ መጋቢት 30 2011ማስታወቂያ
የቡድኑ አባል የሆኑት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በተለይ ለ ዶይቼ ቬለ (DW) እንደገለጹት የጀርመን መንግሥት ከአሁን ቀደም በአውሮጳ ሕብረት በኩል ለአገሪቱ የሚሰጠውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጧል። የኢትዮጵያ የምርጫ ሕግ ማሻሻያ አዋጅ መጽደቅንም ተከትሎ ሕጋዊ ምዝገባ ሳያካሂዱ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ፓርቲዎች ላይ ቁጥጥር እንደሚጀመርም ወይዘሪት ብርቱካን አመልክተዋል። የፖለቲካ ፓርቲዎች የፋይናንስ ድጋፍ የኮታ ድልድልን በተመለከተም በኅብረተሰቡ ውስጥ ጥሩ መሠረት ያላቸው እና የዲሞክራሲያዊ ሂደቱን በደንብ ሊያግዙ የሚችሉ ድርጅቶች የተሻለ ድጋፍ እንደሚያገኙም ጠቁመዋል። ዝርዝሩን እንዳልካቸው ፈቃደ አጠናቅሮታል::
እንዳልካቸው ፈቃደ
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ