የኢትዮጵያ ለዉጥና የክራይስስ ግሩፕ ዘገባ
ማክሰኞ፣ የካቲት 19 2011ማስታወቂያ
ኢትዮጵያ የጀመረችዉ የፖለቲካ ለዉጥ ከከሸፈ መዘዙ ከኢትዮጵያ አልፎ የአካባቢዉን ሐገራት የሚያብጥ ቀዉስ እንደሚያስከትል ክራይስስ ግሩፕ የተሰኘዉ አጥኚ ተቋም አስጠነቀቀ። ዓለም አቀፉ አጥኚ ተቋም እንደሚለዉ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ የሚመሩት የለዉጥ ርምጃ የጎሳ ግጭትን ጨምሮ አሁንም በርካታ ፈተናዎች ተጋርጠዉበታል።የለዉጡ ሒደት ከተሰካ ለአካባቢዉ ሐገራት ጠቃሚ፣ ለመላዉ አፍሪቃ ደግሞ አብነት በመሆኑ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ሊደግፈዉ እንደሚገባ የተቋሙ ጥናት ይጠይቃል።
ገበያዉ ንጉሴ
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ