የኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ በበርሊን
ዓርብ፣ ሚያዝያ 19 2004ማስታወቂያ
በጀርመን መዲና በርሊን የተሰባሰቡ ኢትዮጵያውያን ፣ የኢትዮጵያን መንግሥት በመቃወም ዛሬ ሰልፍ ወጡ ። ሰልፈኞቹ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚወስዳቸውን እርምጃዎች የሚቃወሙ ልዩ ልዩ መፈክሮችን እያሰሙ፣ ከጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ተነስተው በ ህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አድርገው ወደ መራኂተ- መንግሥቷ ምክር ቤት ነበረ ያቀኑት። እዚያም እንደደረሱ ተቃውሞአችውን ያሰፈሩበትን ደብዳቤ ለጀርመን መንግሥት አስረክበዋል ። ሰልፉን በመከታተል ላይ ከነበረው ከበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ጋራ ስለ ሰልፉ ዓላማና ሂደት በስልክ የተደረገው ቃለ ምልልስ እነሆ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ሂሩት መለሰ