የኢትዮጵያውያን ስደተኞች ሞት በካሌ ፈረንሳይ
ዓርብ፣ መጋቢት 19 2006ማስታወቂያ
ፈረንሣይን በስተሰሜን ከእንግሊዝ የምታዋሰነው የካሌ ደሴት ስደተኞች ወደ ታላቅ ብሪታንያ ለመግባት እንደ መሸጋገሪያ የሚጠቀሙባት የወደብ ከተማ ናት፡፡ በዚህች ወደብ በኩል ሰደተኞች በምግብ፣ በአልባሳት ና በቁሳቁስ መጫኛ ካሚዮኖች ተደበቀው ያለ ሕጋዊ የጉዞ ሰነድ ወደ እንግሊዝ ለመሻገር ይሞክራሉ። ከጊዜ ወደ ግዜ የሁለቱ አገራት ደንበር ጠባቂ ፖሊሶች ጥብቅ ክትትላቸውን ቢያጠነክሩም አሁንም በርካታ ሰደተኞች በአደገኛ ጉዞ ድንበር ለማቀረጥ ሲሞክሩ ሕይወታቸውን የሚያጡበት አጋጣሚ በርካታ እንደሆነ ይነገራል፡፡ ባሳለፈነው የካቲት ና በያዝነው የመጋቢት ወር ኢትዮጵያውያንና የሌሎች አገራት ስደተኞች በካሌ በተለያዩ አደጋዎችና ባልታወቁ ምክንያቶች ህይወታቸውን አጥተዋል ፡፡ ከዚህ ቀደም ወደ እንግሊዝ በሚያሻግረው መሿለኪያ አቅራቢያ ይገኝ የነበረው የሳንጋት የሰደተኞች መቀቢያ ጣቢያ እ.ጎ.አ በ2002 ከተዘጋ በኋላ በአካባቢው ቃሚ የስደተኞች መቀበያ ጣቢያ አለመኖር የሰደተኞችን ሕይወት አስቸጋሪ እንዳደረገው ዶቼቬለ ያነጋገራቸው ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ገልፀዋል ።ዝርዝሩን ሃይማኖት ጥሩነህ ከፓሪስ ልካልናለች
ሃይማኖት ጥሩነህ
ሂሩት መለሰ
ነጋሽ መሃመድ