የኢትዮጵያዊው ተጠርጣሪ የሕገ ወጥ ሰው አዘዋዋሪ ጉዳይ
ማክሰኞ፣ ሐምሌ 21 2007ማስታወቂያ
የማያስተማምኑ ጀልባዎቻቸው እየሰመጡ የትም ወድቀው የሚቀሩበት ድርጊት አሳዛኝ ክስተት መሆኑን በደቡብ ኢጣልያ የምትገኘው የሲሲሊ ደሴት ዋና ከተማ ፓሌርሞ የሚገኘው ፀረ ማፍያ ምርመራ ቡድን መምሪያ አስታወቀ። የምርመራው ቡድን አክሎ እንዳመለከተው ግን፣ በተቀነባበረ እና በሕገ ወጥ መንገድ ሰዎችን የሚያዘዋውሩ ወንጀለኞች ለስደተኞቹ ሞት በዋነኝነት ተጠያቂዎች ናቸው። በዚህም የተነሳ የፓሌርሞ ፀረ ማፍያ ምርመራ ቡድን ስደተኞችን በሕገ ወጥ መንገድ ያዘዋውራል ብሎ በጠረጠረው አንድ ኢትዮጵያዊ ላይ በወቅቱ ምርመራ በማካሄድ ላይ ይገኛል።
ተኽለእዝጊ ገብረየሱስ
አርያም ተክሌ
ሸዋዬ ለገሠ