የኢትዮጵያዉያን የባህል እና የፖለቲካ መቻቻል እንዴት ይታያል?
እሑድ፣ መጋቢት 1 2005መቻቻል ወይም ማስተዋል የዛሪን ሳይሆን የነገን የማለም፤ ከምንም በላይ ራስን የመግዛት ነፀብራቅ መሆኑ ብዙዎች ይስማሙበታል። ይህ ደግሞ ከዉስጡ ከተገኙበት ማህበረሰብ ብሎም ካደጉበት፣ ከጎለመሱበት ሊቀዳ እንደሚችል ይገመታል። ኢትዮጵያዉያን ትሁትነት፣ ታጋሽነት፣ እንግዳ ተቀባይነት በብዙ ጸሃፊዎች ይጠቀሳል። ይህ ታጋሽነት እና ትህት እስከ ምን ደረስ ተብሎ ሲፈተሽ ደግሞ በተለይ እርስ በርስ ባለ ግንኙነት ላይ ጥያቄ የሚያስነሱ ክስተቶች ሲያጋጥም ይስተዋላል። የመቻቻል ባህል በተለይ ብዙዎች እንደሚሉት ከ60ዎቹ ወዲህ ባለዉ ትዉልድ እየተሸረሸረ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። መንግስት ተቃዋሚዎቹን የሚይዝበት እና መገናኛ ብዙሃን ላይ የሚወስደዉ ርምጃ ሲታይ፤ በአንፃሩ ተቃዋሚዎች አፀፋ። ከተለያዩ ድረ ገፆች የሚነበቡ ፅሁፎችም ለዚህ ማሳያ ይጠቀሳሉ። ግለሰቦች የወጡበት ኅብረተሰብና ባህል ነፀብራቅ ናቸዉከተባለ፤ የኢትዮጵያዉያን የባህል እና የፖለቲካ መቻቻል እንዴት ይታያል? በያዝነዉ ሳምንት ዶይቼ ቬለ ሶስት እንግዶችን ጋብዞ አወያይቷል። በሰሜን አሜሪካ ነዋሪ የሆኑት የስነ-ልቦና እና የስነ-አዕምሮ ባለሞያ፤ ወ/ሮ አበባ ፈቃደ፤ በአዳማ ነዋሪ የሆኑት እና በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ለአስራ አምስት አመት አገልግለዉ በጥሩታ ላይ የሚገኙት የህብረተሰብ ጉዳይ ጥናት ምሁሩ ዶ/ር ገመቹ መገርሳ፤ እንዲሁም በአፍሪቃ ህብረት ጉዳዮች ላይ አማካሪ የሆኑት አቶ መሃሪ ታደለ ናቸዉ። ሙሉዉን ዉይይት ያድምጡ!
ሸዋዪ ለገሰ
አዜብ ታደሰ