የኢትዮጵያዉያን ተቃዉሞ በለንደን
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 27 2008ማስታወቂያ
ሠልፈኞቹ የኬንያ መንግሥት ከኢትዮጵያ ሸሽተዉ ሐገሩ የገቡ ስደተኞችን ለኢትዮጵያ መንግሥት አሳልፎ ሰጥቷል፤ የብሪታንያዉ ማሰራጫ ጣቢያ BBC ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚፈፀመዉን በደል ተከታትሎ አልዘገበም በማለትም ወቅሰዋል።የኢትዮጵያ መንግሥት የተቀናጀ ማስተር ፕላን ያለዉን ዕቅድ በተቃወሙ ሰዎች ላይ የወሰደዉን እርምጃ በመቃወም ለንደን ዉስጥ የአደባባይ ሠልፍ ሲደረግ በሰወስት ሳምንት ዉስጥ የዛሬዉ 3ኛዉ ነዉ።ነጋሽ መሐመድ የለንደን ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕን አነጋግሮታል።
ድልነሳ ጌታነሕ
ነጋሽ መሐመድ
ማንተጋፍቶት ስለሺ